Description
by Dr Shimelis Wondimu
የመጽሐፉ አሳብ የሕይወት ምስክርነት ነው። ለትምህርት የተጻፈ እንደመሆኑ በአንድም በሌላ በክርስትና የሩጫ ጉዞዬ ላይ አሻራችሁን ያስቀመጣችሁ በሙሉ ጌታ ይባርካችሁ ማለትእወዳለሁ። የመከራችሁኝ ያፅናናችሁኝና ያበረታታችሁኝ በሙሉበተለይም ባለቤቴ ሔዋንና ልጆቼ ንጹሕ ሽመልስና ክርስቲያን ሽመልስ ጌታ ይባርካችሁ።
በቤሪያና በሞርኒንግ እስታር የቴሌ ኮንፍራንስ አገልጋዮችእንዳገለግልና በጸጋ እንዳድግ እድል ስለሰጣችሁኝ ጌታ ይባርካችሁ። እንዳገለግል መድረኮቻችሁን የሰጣችሁኝ ፓስተር አቦማ፣ ፓስተር መንግሥቱ እና ፓስተር ዶ/ር ሙሉዓለም ጌታ ይባርካችሁ እላለሁ። እንዲሁም በርታ ያላችሁኝ ፓስተር አየለ፣ ወንድም ሳሙኤል ቶሎሳ (ሳሚ) በተጨማሪ የጽሑፌም የትምህርቴም የስብከቴም ተከታታይ የሆናችሁ በሙሉ ጌታ ይባርካችሁ።
በመጨረሻም ተጽፎ ከመቼ መቼ በመጽሐፍ መልክ ተጠርዞ ለሕዝብ ይደርሳል የሚለውን ናፍቆት ሥጋ እንዲለብስ
ያደረገውን ወንድም ዓለማየሁ ማሞን ከልብ አመሰግናለሁ። በጥቅሉ በዚህ ጽሑፍ ላይ ለትምህርቴ ወደ ጌታ እንድቀርብ ከፍተኛ ሚና የተጫወታችሁ በሙሉ ጌታ ይባርካችሁ እላለሁ ። በመጨረሻም ይህን የምስክርነት መጽሐፍ ለባለቤቴ ሔዋንና ለልጆቼ ንጹሕና ክርስቲያን ማስታወሻ ይሁንልኝ። እወዳችኋለሁ።
ሽመልስ ወንድሙ
Reviews (0)
You must be logged in to post a review.
AddisBooks Ads








Reviews
There are no reviews yet.