Author's Books
Deciding What to Read Next?
Description
Born in Deder, Ethiopia, the author completed his primary and middle school education in his hometown and finished high school in Dire Dawa. He moved to the United States in 2002 through the DV Lottery and has since devoted his life to Christian ministry, teaching, and writing. He earned his Ph.D. in theology through Christ Glory Graduate School, an Ethiopia-based online institution, and also studied at IICM Bible College and Theological Seminary in Florida. He currently leads the Amharic online ministry Clean Christians for Christ and has written five books, including The Weight of Salvation, inspired by his desire to share God’s profound love for humanity.
በደደር ከተማ ተወልጄ ያደኩ ስሆን ትምህርቴንም ከ1-10 በዛው ከተማ ተከታትያለሁ። በመቀጠል 11ኛ እና 12ኛን በድሬዳዋ ከተማ ሀይስኩል ጨርሼ። በመሰረተ ክርስቶስ ቤ/ክ መጋላ አጥቢያ መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናትና በማስጠናት አገለግል ነበር። በ2002, በእግዚአብሔር ፀጋ፣ ወደ አሜሪካ ያመጣኝን የዲቪ (ዲይቨርሲቲ ቪዛ) ሎተሪ በማሸነፍ እድለኛ ሆንኩ። በካምብሪጅ፣ ማሳቹሴትስ፣ ለብዙ ዓመታት ስኖር በንቃት “በቦስተን የኢትዮጵያ ክርስትያኖች ህብረት ቤተክርስቲያን።” ማስተማር፣ መስበክ፣ ክርስቲያናዊ ግጥሞችን እና ጽሑፎችን መጻፍን ጨምሮ አገልግያለሁ። በኦንላይን ፕሮግራሞች ትምህርቴን በማስፋት። መቀመጫውን ኢትዮጵያ አድርጎ በክራይስት ግሎሪ የድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት ተምሬያለሁ፣ እንዲሁም በፍሎሪዳ በሚገኘው አለም አቀፍ የቤተክርስቲያን አስተዳደር (IICM) የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ እና የነገረ መለኮት ሴሚናሪ ትምህርቴን ተከታትያለሁ። በነዚህ ተቋማት የፍልስፍና ዶክተር (Ph.D.) ዲግሪ በጌታ እገዛ አግኝቻለሁ። በአሁኑ ጊዜ በአማርኛ “ንፁህ ክርስቲያን ለክርስቶስ” በተባለ የመስመር ላይ አገልግሎት እያገለገልኩ ነው። በጌታ ፀጋ 5 መፅሐፎችን ፅፌአለሁ 5ተኛው “የመዳን ሸክም “The Weight Of Salvation” ነው። ለመጻፍ ያነሳሳኝ፣ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር፤ ያወኩትን ለማሳወቅ ነው። ተባረኩ!!
Review
Customer Reviews
For This Month







Write A Review