Sew Bertu Beret Kentu ሰው ብርቱ ብረት ከንቱ by Tilahun Fanta
$22.00
Sew Bertu Beret Kentu ሰው ብርቱ ብረት ከንቱ by Tilahun Fanta .
Addis Books!
Description
Sew Bertu Beret Kentu ሰው ብርቱ ብረት ከንቱ by Tilahun Fanta
አሪፍ ታሪክ ነጋሪ፥ ወግ አጋሪ፥ ከራስ ጋር አነጋጋሪ መጽሃፍ ነው። በጨዋታ ለዛ የማህበራዊ ሂስ አቀራረቡ ልብ አይቆረቁሬ ነው። መጽሃፉ አንኳር የአገራችንን ችግሮች የተንጸባረቀበት ነው። ስለትምህርት ጥራት፥ ስለሙያ እውቀት አስፈላጊነት እና ፈተናው፥ ስለ ባላገሩ ኑሮ ምስል፥ ስለ ፖለቲካችን ገመና፥ አማራው በሽግግር ዘመን ከክልሉ ውጪ ስላየው፥ አበሳ፥ ስለንግድ እና የንግድ ፈቃድ ስንክሳር፥ ስለህዝባችን የ’ምትሃት’ መፍትሄ ፈላጊነት ምኑ ቅጡ! ደራሲው ከረገጠው መሬት ሁሉ እግሩ ወርቅ ይዞ ነው የተነሳው።
አባ ታድያ አለንጋቸው አይጣልባችሁ፤የልጅ ፍቅር ጌታ የሰጣቸው አይመስለኝም፡፡ ላለመገረፍ ጎንበስ ብሎ ጫማ መሳም፣ መስቀል መሳለም፣ ወጥቶ ፊደል ማስቆጠር ዋናዎቹ ነበሩና ሁሉንም ፈጽሜ ከዛ አለንጋቸው ለማምለጥ በጠዋቱ ነበር ጥረቴን የጀመርኩት፡፡
በሦስት ወር ገደማ እግዚአብሔር ራሱን በአልፋ ጀምሮ በኦሜጋ እንዲጨርስ አባም በሚያስተምሩበት ዘይቤ ፊደልን ከሀ – ፖ ለየሁ፡፡ ማንና ማን እንደወለዷቸው ሳላውቅ ዲቃላ ፊደላት የምትሏቸውንም አወቅኋቸው፡፡ ቁጥርን በግዕዙም በፈረንጁም ለመድኩት፡፡
አባ ፈለገ ሰይጣን ከመጣና ካጣላን እንደማያስተርፉኝ አውቄ ሁሌ በጥንቃቄ ብማርም ቀኔ ደረሰችና ፊደል እንዳስቆጥር ጥግ ሆነው እግራቸውን አንፈራጠው ጭራቸውን እያወዛወዙ ተነሥ ሲሉኝ እንደሌላው ቀን ኮራ እንዳልኩ ወጥቼ
“ሀ – ግዕዝ” ስል ቤቱን የሞላው ተማሪ ደስ በሚል ቅላጼ “ሀ – ግዕዝ” ብለው ተከተሉኝ፡፡
ሁ – ካብዕ
ሂ – ሳልስ
ሃ – ራብዕ
ሄ – ሐምስ
ህ – ሳድስ
ሆ – ሳ ብ ዕ እያልኩ የመጀመርያ መስመሩን አስቆጠርኩ፡፡ ሁለተኛውን መስመር ጀምሬ
ለ – ግዕዝ
ሉ – ካብእ
ሊ- ሳልስ
ላ – ራብዕ
እንዳልኩ ያልጠበኩት ነገር ተፈጠረ፡፡ ከፊደሉ ጀርባ ያለው የአፈር ቤት ግድግዳ ከኋላ የተሰነጠቀ ነበርና አባ አዲስ የገዙት ፊደል ማስቆጠርያ “ላ” ፊደልን በጣም ተጭኜአት ኖሮ ግድግዳው ውስጥ ሰምጣ ቀረች፡፡
ከመቅጽበት ትንሸዋ ልቤ ደለቀች፡፡ በድንጋጤ እኔ ሌ- ሐምስ ባልልም ተማሪው በልምድ ሌ- ሐምስ በማለት እየቆጠረ ነበር፡፡ አባ ሁኔታውን ከማስተዋላቸው በፊት ማስቆጠሪያ ዱላዬን በአየር ላይ ለቅቄ ከቄስ ትምህርት ቤቱ በሩጫ ወጥቼ ንፋስ በጆሮዬ እያፏጨ ቤት ደረስኩ፡፡ እናቴ በሁኔታዬ ተገርማ ምን እንደተፈጠረ ሳትጠይቀኝ በፊት ለፈለፍኩ፡፡
እናቴ በዚህ ሁኔታ በነጋታው ከመለሰችኝ እንደማያስተርፉኝ ስለገባት ሳምንት ቆየችና አሁን ይረሳሉ ወይም ይራራሉ በማለት “ፊደል እገዛለሁ እንጂ ከጓደኞችህ ተለይተህ ሳትማር እንዴት ትቀራለህ ?” ብላ የወር ክፍያውን አንድ ብር ይዛ እኔን አስከትላ እሷ ፈራ ተባ እያለች እኔም እየተንቀጠቀጥኩ አባ ዘንድ ቀረብን፡፡
…….
Reviews (0)
You must be logged in to post a review.
AddisBooks Ads






Reviews
There are no reviews yet.