Cart

  • Home
  • Fiction

Altezewawerechim አልተዘዋወረችም by Alex Abreham

$18.00

Altezewawerechim አልተዘዋወረችም by Alex Abreham.
Addis Books!
January 4, 2024 Amharic 238 pages

Authors

Meet the Author

Alex Abreham አሌክስ አብርሃም

Books By Alex Abreham አሌክስ አብርሃም View All
Anfersem Anetadesem አንፈርስም አንታደስም by Alex Abreham
Anfersem Anetadesem አንፈርስም አንታደስም by Alex Abreham
Enat Feker Hager እናት ፍቅር ሐገር by Alex Abreham
Enat Feker Hager እናት ፍቅር ሐገር by Alex Abreham
Altezewawerechim አልተዘዋወረችም by Alex Abreham
Altezewawerechim አልተዘዋወረችም by Alex Abreham
Doctor Ashebir ዶክተር አሸብር by Alex Abreham
Doctor Ashebir ዶክተር አሸብር by Alex Abreham

Description

Altezewawerechim አልተዘዋወረችም by Alex Abreham

ፍቅር ሁሉ ፍቅር አይደለም። በደፈናው አፈቀርን ወይም ተፈቀርን እንበል እንጅ ሰዎች ምናችንን በምን ምክንያት እንደወደዱልን በእርግጠኝነት መናገር የሚቻል ነገር አይደለም። ሰዎች ከማንነት በላይ ለአካላዊ ውበት በፍቅር ሊወድቁ ይችላሉ፤ ምናልባትም ይህ ለራሳቸውም አይገባቸውም ይሆናል። ከነጭራሹ «ወደድናችሁ» ያሉን ሰዎች እንደወደዱን ማረጋገጫችንስ ምንድነው ? ትዳር ? ስጦታ? ቃልኪዳን? ለእኛ የሚከፍሉት መስዋዕትነት? በመኖር ብቻ የሚመለስ ጥያቄ ሳይሆን አይቀርም። በዚህ መፅሐፍ ከነመኖራቸው ትዝ የማይሉን ጥቃቅን ስሜቶች ስንጥቃቸው እየሰፋ ሕይዎትን ለከባድ ምስቅልቅል ሲዳርጉ እናያለን።

«ምናለበት» ተብለው ችላ የተባሉ እንደውም እንደበጎ ነገር የሚታዩ ጉዳዮች በጥልቀት ሲቃኙ ያላቸውን አደገኛ ስር እንመለከታለን። በሕይዎት ውስጥ « ቁጭ ብለን የሰቀልነውን ቁመን ማውረድ ሲያቅተን» ሌሎች ድሎት ያሉት ነገር ለሌላው መከራ ሲሆኑ ፣ እንታዘባለን። ፅናት፣ ፍቅር ፣ ስደት ፣ናፍቆት ፣ዓላማ ፣ ሐዘን ፣ደስታ ፣ በውብ ትረካ ተሰድረው እናገኛቸዋለን። እንደቀላል የልጅነት ሁዳዳችን ላይ የተጣለች ቅንጣት የቃል ዘር በኋለኛው ዘመናችን ዛፍ ሁና ጥላዋን በአኗኗራችን ላይ ስታጠላ እንታዘባለን። በመጨረሻም መፅሐፉን ስንከድን የራሳችንን ሕይወት ከፍተን መመልከት እንጀምራለን።

ደራሲ አሌክስ አብርሃም በማህበራዊ ድረገፆች ፣ በመፅሔቶች በሚፅፋቸው በሁሉም ስራዎቹ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘ ወጣት ደራሲ ነው። ከዚህ በፊት ዶ/ር አሸብርና ሌሎችም ፣ እናት ፍቅር ሐገር፣ ዙቤይዳ ፣ አንፈርስም አንታደስም ፣ ከዕለታት ግማሽ ቀን እንዲሁም ይህ አልተዘዋወረችም የሚል ስራው ተጠቃሽ ናቸው።

መልካም ንባብ።

 

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “Altezewawerechim አልተዘዋወረችም by Alex Abreham”
AddisBooks Ads
ምርጥ ክላሲካል ሙዚቃ Ethiopian Music Instrumental - Ethiopian Music