888
This book contains the gematria of the Geez alphabet. There are 26 letters of Geez and each letter has a number that it represents and can reach up to 800. This 888 book uncovers the spiritual and scientific codes hidden in the Geez alphabet through Geez gematria. The author of the book is Dr Rodas Tadese Abebe and he has published 25 research books.
አንባብያን 888 የሚለውን ርእሱን በሚያዩበት ጊዜ ምን
ይኾን? ለምን ይኽነን ርእስ መረጠው? ሳይሉ እንደማይቀሩ እገምታለኍ፡፡ ይኸውም ከ6 ዓመታት በፊት ላይ "ቀመር 888 እና መጽሐፍ ቅዱስ" በሚል ርእስ "888" ከወሩ፣ ከቀኑ፣ ከዓመቱ ጋር
መገጣጠሙን በማሰብ በ2008 ዓ.ም. በቀን 8 በ8ተኛ ወር ላይ በፌስቡክ ላይ ዘርዘር አድርጌ በመጻፍ ለአንባብያን አንድ ጽሑፍ አጋራኊ፡፡ ያነንም ጽሑፍ ብዙዎች በጊዜው አንብበውት ነበር፡፡
የሚገርመው ነገር ከ6 ዓመታት በኋላ በ2014 ዓ.ም. ልክ ያነን ጽሑፍ በለቀኩበት ዕለት በ8ኛው ወር በሚያዝያ፣ በ8ተኛው ቀን፣ በ8ኛው ሰዓት ላይ 24ተኛው መጽሐፌ "ማዛሮት" በድምቀት ተመረቀ፡፡ በዚያ የመጽሐፍ ምረቃት መርሐ ግብር ላይ ኾኜ ይኽነን ግጥጥሞሽ ችላ ብዬ አልተመለከትኩትም፡፡
ይልቁኑ እንደ ትልቅ ምልክት በማሰብ በዚያው መጽሐፌ በሚመረቅበት ዕለት ይኽነን የ888 ምስጢርን፣ ይልቁኑ በግእዝ ፊደላት ውስጥ ያሉትን አቅማራትን፣ ምድራዊና ሰማያዊ ምስጢር ለአንባብያን አዘጋጅቼ ለማቅረብ ለራሴ ቃል ገባኊ፡፡
የወርቅ ዘንግ መጽሐፍን ለአንባብያን ያበቃው በቀመር 7 ላይ ምርምር የሚያደርገው መምህር መስፍን ሰሎሞንም ይኽነን
ዕውቀት በልቤ ይዤው እንዳልቀር ይልቁኑ ለትውልድ በጽሑፍ እንዳስተላልፈው አብዝቶ ይጠይቀኝ ስለነበር እንድጽፈው አንዱ ምክንያት ስለኾነኝ በዚኹ አጋጣሚ አመሰግናለኊ፡፡
የትምህርት ታላቁ ግብ አስቀድሞ ራስን ማወቅ ከዚያም በዕውቀት፣ በጥበብ ብርሃንነት ሐሰትን ከእውነት፣ ብርሃንን ከጨለማ መለየት፣ ሀገርን በቅንነት፣ በእውነተኛነት ማገልገል እንጂ በአንድ የማሠልጠኛ ተቋም ውስጥ ገብቶ የመመረቂያ ልብስ
ለብሶ፣ የምስክር ወረቀት መቀበል ብቻ አይደለም፡፡
በመኾኑም የኹላችኹም የኢትዮጵያውያን ሀብት የኾነው
ይኽነን ፊደል ለብዙ ሺሕ ዘመን የያዘውን ታላቅ ጥበብና ሰማያዊ ምስጢርን በዕውቀት፣ በማስተዋል መረዳት ስትዠምሩ ያን ጊዜ ፊደላችኹን መውደድ፣ ማክበር፣ መጠበቅ ትዠምራላችኊ፡፡
በዚኹ አጋጣሚ ፊደላችን የያዘውን ታላቅ ምስጢር ዐውቀው በምቀኝነት ለማጥፋት ከሚተጉ ከክፋት ሰራዊት፤ ዳግመኛም አለማወቅ ድቅድቅ ጨለማ ነውና ሳያውቁትም
በሞኝነት ፊደላቱን ለማጥፋት ከአጥፊዎች ጋር ከሚተባበሩ ጠብቃችኊ ለመጪው ትውልድ የተቀበላችኹትን አደራ እንድታሸጋግሩት ወደ እውነተኛው የጥበብ ብርሃን እንድትደርሱበት ሐሳቤ ነው፡፡
$25.00
ABREN አብረን
Emebet Mengiste's new book -Abren is a beautifully written work of art. Set in Ethiopia, It's a tale of a childhood friendship, love and loss . The story revolves around eight friends who come into each other's life in kindergarten and manage to grow old together. As always her story teaches us to examine ourselves and our relationship with our loved ones, as well as to society. The book also boldly discusses 'taboo' topics such as depression and loneliness which are not frequently brought to attention.
$20.00
Addis Hiwot by Dagmawi Assefa
አዲስ ሕይወት በዳግማዊ አሰፋ Addis Hiwot - A book by Dagmawi Assefa.
Addis Books
Amest Guday አምስት ጉዳይ by Yared Teshome Zelelew
Amest Guday አምስት ጉዳይ by Yared Teshome Zelelew.
Addis Books!
Amharic For Foreigners and the Ethiopian Diaspora
Wanna learn Amharic? This book helps you learn the Amharic language from the very beginning to an intermediate level. It teaches you the alphabet, the punctuation marks, the pronunciation, the grammar, the vocabulary that are basically required to communicate for transportation, shopping, dining at restaurants, and visit Ethiopia and enjoy its diverse cultures!





















